የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ እያካሄደ ነው
ሰንበቴ፣ መስከረም 14/2019 ዓ.ም (ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት )
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት የ2018 ዓ.ም የሥራ እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ ከፅህፈት ቤቱ ባለሙያዎች ጋር እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የ2018 ዓ.ም የኮሙኒኬሽን ሥራዎች አፈፃፀም በዋና ዋና ሥራዎች፣ የተገኙ ውጤቶችና በአፈፃፀም ወቅት የታዩ ተግዳሮቶች የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ አሚን አልይ ለባለሙያዎቹ ገለፃና ማብራሪያ አድርገዋል።
እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት የሥራ እቅድ ለባለሙያዎች ሀላፊው ያመላከቱ ሲሆን
በተለይ በ2018 አ,ም በመልካም አስተዳደር ፣በመንግስት የስራ ሰአት አከባበር ፣በእቅድ ዝግጅት፣ በቸክ ሊስትና በግብረ መልስ አሰጣጥ ፣የባጀት አጠቃቀም ላይ ውይይት እንዲካሄድ ማብራሪያና ገለፃ ሃላፊው አድርገው ባለሙያዎቹም በጥልቀት እየተወያዩ በት ይገኛል
በመድረኩ የፅህፈት ቤቱ ማናጅመንት አባላቶች ፣የፅህፈት ቤቱ ባለሙያዎች፣ ደጋፊ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በሚዲያ ይዘት ማበልፀግ ዝግጅትና ስርጭት ቡድን