ይህ ወረዳ በዚህ ስያሜ መጠራት የጀመረው በደርግ ስርዓተ መንግስት የወረዳዎችና ዞኖች ምስረታ ወቅት እንደሆነና በሰሜን ሸዋ ክፍላ ሀገር ይፋትና ዱሙጋ አውራጃ ኤፍራታና ጅሌ ወረዳ በመባል እንደምትታወቅ የተለያዩ በጽሁፍ የሚገኙ ድርሳኖችና መጻጽፎች እንዲሁም አፈታሪኮች ያሰረዳሉ፡፡
ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ይህን አሁን የምትጠራበትን ስያሜ ራሷን ችላ ያገኘችው ከ1986 ዓ/ም መባቻ ላይ ከኤፍራታና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ከተለየችበት ጊዜ አንስቶ ሲሆን የወረዳዋ ዋና ከተማ ሰንበቴ በማድረግ ተመሰረተች፡፡ በ1987 ዓ/ም የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ራሱን ችሎ በተመሰረተበት ወቅት ከአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጋር በመቀላቀል አርጡማ ጅሌ የሚል ስያሜ ተስጥቷት እስከ 1993 ዓ/ም መቆየቷም ይነገራል፡፡ የስሟ ስያሜ እንደየወቅቱና ነባራዊ ሁኔታ ሲቀያየር መጥቶ ከ1993 ዓ/ም መባቻ ላይ ከአርጡማ ጅሌ ወረዳ በመለየት ራሷን ችላ ዛሬ ለምትጠራበት ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ስያሜ ላይ ደርሳለች፡፡
እምነትና ቋንቋ
በወረዳዋ ውስጥ ከሚኖረው ማህበረሰብ 99% የሚሆነው የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን 1% የሚሆኑት የተለያየ እምነት ተከታይ እንደሆኑ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ከቋንቋ አንፃር 95% ኦሮሚኛ ተናጋሪ ሲሆኑ 5% አማርኛ ተናጋሪ ናቸው፡፡