የአጣዬ ሆስፒታል እግር ኳስ ክለብ ለፍጻሜ ጨዋታ ማለፉን አረጋገጠ -------------------------- ሰንበቴ:ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም(ጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬሽን) በሰንበቴ ከተማ በድምቀት እየተካሄደ በሚገኘው የ2018 ዓ.ም የክረምት የወጣቶች እግር ኳስ ውድድር በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታው የአጣዬ ሆስፒታል ክለብ ተጋጣሚውን የጨፋ እግር ኳስ ክለብን በፔናሊቲ 7 ለ 6 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የመጀመሪያው ለዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ተፋላሚ አረጋግጧል።
ሁለቱ ቡድኖች ለዋንጫ ጨዋታ ለማለፍ ያደረጉት ፉክክር ከፍተኛ የውድድር መንፈስ የታየበት ነበር። በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ በማድረግ 1 አቻ በሆነ ውጤት እረፍት ወጥተዋል።
በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽም በክለቦቹ መካከል ተመጣጣኝ ፉክክር የታየ ሲሆን ተጨማሪ ግቦችን ማግባት ባለመቻላቸው የጨዋታው መደበኛ ደቂቃ ተጠናቋል።
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የፔናሊቲ እድል የአጣዬ ሆስፒታል ክለብ 7 ለ 6 በሆነ የግብ ልዩነት የጨፋ እግር ኳስ ክለብን በማሸነፍ ለፍጻሜ ጨዋታ ማለፉን አረጋግጧል።
በቀጣይ መርሃ ግብር ቢፍቱ እግር ኳስ ክለብ እና ጅዳ እግር ኳስ ክለቦች ለፍጻሜ ለማለፍ የሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ የሚጠበቅ ሲሆን ከሁለቱ አሸናፊ የሚለየው ክለብ ከወዲሁ የፍጻሜ ጨዋታውን መቀላቀሉን ካረጋገጠው ከአጣዬ ሆስፒታል ጋር የውድድሩ ሻምፒዮና ለመሆን ይፋለማል።