ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አዲስ ዘመናዊ ድህረ ገጽ አስመረቀ ------------------------------- ሰንበቴ:ነሐሴ07/2018 ዓ.ም(ጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬሽን)
ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሙኒኬሽን በወረዳው እየተከናወነ ያለውን የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለህብረተሰቡ በተደራጀ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል አዲስ ዘመናዊ ድህረ ገጽ በዛሬው እለት አስመርቋል።
ተቋሙ ያስመረቀው አዲስ ድህረ ገጽ ተቋማዊ መረጃዎችን በፍጥነት እና በብቃት ለማሰራጨት ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
የምረቃ ስነ-ሰርዓቱ የጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ ጽ/ቤቶች የተውጣጡ ባለሙያዎች እና የጽ/ቤቱ ሰራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሚን አልይ በምረቃ መርሃ-ግብር ላይ ባደረጉት የመክፈቻ "ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አማራጮችን መጠቀም የህዝብን የመረጃ ባለቤትነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው" ብለዋል።
በመሆኑም በወረዳው የሚከናወኑ ሁለገብ የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ለህብረተሰቡ በወቅቱና በትክክል እንዲደርስ የተጀመረው የዲጂታል ሚዲያ ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።
በምረቃው ስነ-ሰርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከቢር ሀሰን በበኩላቸው ጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ወቅታዊ መረጃዎችን ለህዝቡ ተደራሽ በማድረግ እና ጠንካራ የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በመስራት ረገድ በወረዳው እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ከቢር አያይዘውም ተቋማት የሚሰሯቸውን ስራዎች ግልጽነት ባለው መልኩ ለህብረተሰቡ በማድረስ የሰላም እና የልማት ስራዎችን ማፋጠን እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የድህረ ገጹን ቴክኒካዊ አሰራር እና ይዘት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የድህረ ገጹ አልሚ አቶ ኑሩ አህመድ ድህረገፁ የወረዳውን ታሪካዊ ዳራ፣ ባህላዊ እሴቶች፣ የቱሪስት መስህቦች፣ የትምህርት፣ የጤና እና የግብርና የመሳሰሉ መረጃዎችን ያካተተ መሆኑን አስረድተዋል።
በተጨማሪም በወረዳው ያለውን የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ከህብረተሰቡ መረጃ በመሰብሰብ እና በመተንተን የዳሰሳ ጥናት ለማካሄድ እንዲያስችል ተደርጎ መሰራቱን አቶ ኑሩ በገለጻቸው አብራርተዋል።
የመርሃ-ግብሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ድህረ ገጽ አልምቶ ወደ ስራ ማስገባቱ ከዲጂታል አለም ጋር እራሱን እያዘመነ መምጣቱን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።ተሳታፊዎቹ አክለውም ዛሬ የተመረቀው ድህረ-ገፁ የመረጃ ክፍተቶችን በመሙላት ወረዳውን የበለጠ ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል ይፈጥራል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ህብረተሰቡ የተቋሙን ድህረገፁ በመጠቀም የተለያዮ መረጃዎችን ማግኘት የሚችል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ድህረገፁ ከዛሬ ጀምሮ በይፋ አየር ላይ የዋለ መሆኑ ታውቋል።
👇http://www.jillecommunication.gov.et/