አዋይቱ ፉል ዉሃ በዱላ፣ በወ/ሌንጫ እና በመረዋ አደሬ ቀበሌ አዋሳኝ ቀበሌዎች በ4 ተራሮች መካከል የሚገኝ ሲሆን ከሰንበቴ በግምት 4ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ፍልዉሃ በተፈጠሮ ክስተት የተፈጠረ ሲሆን በጣም ከሞመቁ የተነሳ አካባቢዉን በጭስ ስለሚሸፍን ለአካባቢዉ ልዩ ዉበት ሰቶታል፡፡ በአካባቢዉ አጠራር አዋይቱ የሚለዉ ከኦሮምኛ ቋንቋ ኦአ (o’aa) ከሚለዉ የመጣ ሲሆን ትረጉሙም ሙቅ የሞቀ ማለት ነዉ፡፡ ይህ ፍልዉሃ ከመሬት ዉስጥ የሚወጣ ሲሆን 3 ትልልቅና 6 ትንንሽ የእንፋሎት መዉጫዎች አሉት፡፡ በነዚህ ቀዳዳዎች የሚወጣዉ ሃይለኛ ነጎድጓዳማ ድመፅ ከፈተኛ ነዉ፡፡የዉሃዉ ሙቀት በመሳሪያ ባይለካም ከሙቀቱ የተነሳ ወደ ዉሃዉ የሚያስጠጋ አይደለም፡፡
ፍል ዉሃዉ የሚገኘዉ በአራት ተራሮች መካከል ከሰንበቴ ከሚመጣዉ የቀቢ ወንዝና ከአጣዬ ከሚመጣዉ የአጣዬ ወንዝ መጋጠሚያ የዉስጥ አንግል ላይ፣ረግረጋማና ዛፎች ባሉበት እንዲሁም ከሞቀዉ ዉሃ በሚመጣ እንፋሎት በጭስ መልክ በታፈነ አካባቢ ነዉ፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን በአንድ ቦታና በአንድ ጊዜ ማየት ተፈጥሮን ለሚያደንቁ ከፍተኛ የመንፈስ እርካታን ይሰጣል፡፡
ፍልዉሃዉ በዘመናዊ መልክ ለምቶ አገልግሎት ባይሰጥም ባለበት ሁኔታ ህብረተሰቡ ለተለያዩ ነገሮች ይጠቀሙበታል ከነዚህም መካከል፡ ፍሉን ዉሃ ከወረጅ/ቀዝቃዛ ዉሃ ጋር በመበረዝ ሰዉነታቸዉን የሚታጠቡ ሲሆን እንዲሁም ጭሱን ደግሞ ይታጠኑበታል፡፡ይህም የሚሆንበት ምክንያት ከተያዩ በሽታዎች እንፈወሳልን የሚል እምነት ስላላቸዉ ነዉ፡፡