አርቆ ማየት አልቆ መስራት" በሚል መሪ ቃል በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የ2018 ዓ/ም የፓርቲ እና የመንግስት ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማና የ2019 የእቅድ ኦረንቴሽን መድረክ መካሄድ ተጀመረ።
ሰንበቴ ፣ መስከረም 11/2019 ዓ,ም ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን
በወረዳው የሚገኙ ስቪል ሰርቫንት መንግስት ሰራተኛ የስራ ሂደት አስተባባሪዎች ፣ የቀበሌ አመራርና ባለድርሻ አካላቶች በተገኙበት የ2018 ዓ.ም የፓርቲ እና የመንግስት የስራ አፈፃፀም እንዲሁም የ2019 የእቅድ ትውውቅ ኦረንቴሽን እየተካሄደ ይገኛል።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ሰይድ በመድረኩ መክፈቻ እንደገለፁት በንድፈ ሃሳብ የተቀመጠውን አሻጋሪ የእድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ በመተግበር ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ እና በማህበረሰቡ እና በሀገር ልማት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖን እንዲፈጥር "አርቆ የማየት እና አልቆ መሥራት" ቁርጠኝነትን፣ የዓላማ ጽናትን፣ ትብብር ይጠይቃል ብለዋል።
በወረዳው የተከናወኑ የሰላም ፣የልማት ፣የመልካም አስተዳደር ስራዎች ስኬት መሰረቶቹ የሁሉም ባለድርሻ አካላት አሻራዎች መሆናቸውን በመክፈቻ ፕሮግራማቸው ላይ አስታውሰዋል ። የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አሊ መሀመድ ለፕሮግራሙ የተዘጋጀውን አጭር ሰነድ ለተሳታፊዎቹ ገለፃና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
በመድረኩ የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር የጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ኡስማን አልይ እና የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ሰይድ ጨምሮ የወረዳ አመራሮች ፣የስቪል ሰርቫንት መንግስት ሰራተኛ የልማት ቡድን መሪዎች ፣የቀበሌ አመራርና ባለድርሻ አካላቶች ተሳታፊ ሆነውዋል።
በሚዲያ ይዘት ማበልፀግ ዝግጅትና ስርጭት ቡድን