የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የ2018 እቅድ አፈፃጸም እና የ2019 እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ -------------------------- ሰንበቴ: መስከረም 23/2019 ዓ.ም(ጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬሽን)
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የ2018 እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።
የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ኮማንደር መሐመድ አሊ በመድረኩ ተገኝተው እንደገለጹት ባለፈው አመት በወረዳው ሰላም ለማስጠበቅ በተሰራው ከፍተኛ ጥረት በህብረተሰቡ ላይ ተጋርጠው የነበሩ አደጋዎችን መቀልበስ መቻሉን ገልጸዋል።
ኮማንደር መሀመድ አክለውም የባለፈውን ዓመት አፈፃፀም መነሻ በማድረግ የ2019 ዓ.ም የተሻለ እቅድ መዘጋጀቱን ተናግረው በ2019 ዓ.ም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስከበር ተዘጋጅተናል ብለዋል።
የጽ/ቤቱ የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቧል።በዚህም መሰረት ሰላምን ለማስፈን በተደረገው ከፍተኛ ጥረት በህብረተሰቡ ላይ የተጋረጡ የፀጥታ አደጋዎችን መቀልበስ ተችሏል፤ ስጋት የነበሩ የገጠር ቀበሌዎችም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴና ልማት መመለሳቸው ተገልጿል።
ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር በመቀናጀት የፅንፈኛ ቡድኖችን ግጭት የማስቆም ስራ ትኩረት ተሰጥቶታል። በተለይም አሸባሪው "ሸኔ እና ፋኖ"በፀጥታ አካላት ጥንካሬ በወረዳችንን ያሉ ሙሉ ቀበሌዎች የማፅዳት ስራ መሰራቱም በሰነዱ ተመላክቷል።
የቀጠናውን መልክአ-ምድራዊ አቀማመጥ ተንተርሰው የሚፈጸሙ ህገ-ወጥ የሰዎች፣ የገንዘብና የመሳሪያ ዝውውሮችን በጥብቅ የመቆጣጠር ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል።
በመጨረሻም የፖሊስ ተቋሙን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማደራጀት፣ ዘመኑን የዋጁ የፖሊስ አባላትን ማፍራት እና አባላትን በስልጠና ማብቃት የቀጣዩ ዓመት ዋና ዋና ግቦች መሆናቸው ተመላክቷል።