ቢፍቱ ክለብ ተጋጣሚውን ጅዳ ክለብን በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታው በማሸነፍ ለፍፃሜ ጨዋታ ማለፉን አረጋገጠ -------------------------- ሰንበቴ:ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም(ጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬሽን) በሰንበቴ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የ2018 ዓ.ም የክረምት የወጣቶች እግር ኳስ ውድድር የቢፍቱ እግር ኳስ ክለብ እና ጅዳ እግር ኳስ ክለብ ባደረጉት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የቢፍቱ እግር ኳስ ክለብ ጅዳ እግር ኳስ ክለብን በማሸነፍ የፍፃሜ ጨዋታ ማለፉን አረጋግጧል።
በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ክለቦች ግብ ለማስቆጠር ጥረት ቢያደርጉም 0 ለ 0 አቻ ሆነው እረፍት ወጥተዋል።
በሁለተኛው አጋማሽም ሁለቱም ክለቦች የግብ ሙከራዎችን ቢያደርጉም ግብ ሳያስቆጥሩ መደበኛ ሰዓት ተጠናቋል።አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የፔናሊቲ እድል ቢፍቱ ክለብ 5 ለ 4 በሆነ የግብ ልዩነት ጅዳ ክለብን በማሸነፍ ለፍጻሜ ጨዋታ አልፏል።
በቀጣይ ቢፍቱ ክለብ እና አጣዬ ሆስፒታል ክለብ የውድድሩ ሻምፒዮና ለመሆን የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ በጉጉት ይጠበቃል።