ለሴት ሚሊሻ አባላት ሰልጣኞች የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ ------------------------------ ሰንበቴ: ሐምሌ 06/2018 ዓ.ም(ጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬሽን) በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በበጤ ክላስተር ሲሰጥ በነበረው የሚሊሻ አባላት ስልጠና በብቃት ላጠናቀቁ ሴት ሰልጣኞች የማበረታቻ ሽልማት ማበርከቱን የወረዳው ሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ገልጿል።
ጽ/ቤቱ እንዳስታወቀው ስልጠናውን ያጠናቀቁ ሴት የሚሊሻ አባላት ለሀገርና ለወገን ደህንነት እና ሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳዩ ናቸው ብሏል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ፋጡማ ሰይድ በጽ/ቤቱ ስም የተደረገው ማበረታቻ የሴት ሰልጣኞቹን ጥረት በማድነቅ ለነበራቸው ተነሳሽነት እውቅና ለመስጠት አላማ ያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።
ሴቶች ተመራቂ የሚሊሻ አባላት ስልጠናውን በአግባቡ ከማጠናቀቃቸውም በላይ ለሌሎች ሴቶች የጀግንነትና የአርአያነት ተምሳሌት ናቸው በማለት ወ/ሮ ፋጡማ የማበረታቻ ሽልማቱን ምክንያት ጨምረው አስረድተዋል።
በመሆኑም የሴቶችን ሁለተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም ጥሪ ቀርቧል።
በስልጠናው ወቅት የላቀ ብቃት ላሳዩት ሰልጣኞች የተበረከተው የማበረታቻ ሽልማት በሴቶች ዘንድ የተነሳሽነት ስሜት በመፍጠር በወረዳው የፀጥታ ስራ ላይ ያላቸውን ሚና ሊያጠናክር የሚችል መሆኑ ታምኖበታል።