“ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ቃል ከወጣቶችና ሴቶች ጋር ውይይት ተካሄደ ------------------------------------ ሰንበቴ: ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም(ጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬሽን) በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ቃል ከተለያዮ ቀበሌዎች የተውጣጡ ወጣቶችና ሴቶች ቸተሳተፉበት የውይይት መድረክ በዛሬው እለት ተካሂዷል።
በውይይት መድረኩ በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አሚና አሊይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
ወ/ሮ አሚና በመክፈቻ ንግግራቸው "ወጣቶችና ሴቶች ለሀገር ሰላም መስፈን፣ ለልማት መረጋገጥ እንዲሁም ለአገር ሉዓላዊነት መከበር የማይተካ ሚና ያላቸው መሆኑን በማስታወስ የጽንፈኝነትን አስተሳሰብ አምርረው እንዲታገሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ የመነሻ ጽሑፍ በወረዳው የሴቶች ክንፍ ተወካይ ወ/ሮ ሀሊማ አርቦ የቀረበ ሲሆን በአገራዊና በክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ማለትም የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ጽንፈኛ ኃይሎች በመቀናጀት የሀገሪቱን ሰላም፣ አንድነትና የልማት ጉዞ ለማደናቀፍ እየሠሩ መሆናቸውን በሰነዳቸው በዝርዝር ተዳሰዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ወጣቶችና ሴቶች ጽንፈኝነት የልማት ጠላት፣ የሰላም እንቅፋትና የሀገር አንድነት ስጋት መሆኑን በማረጋገጥ በህዝብ አንድነት፣ በጋራ ትግልና በጠንካራ አገራዊ ቁርጠኝነት ማሸነፍ እንደሚቻል አስምረውበታል።
ተሳታፊዎቹ በመጨረሻም የሀገርን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ፣ የተገኙ የልማት ውጤቶችን ለማስቀጠል እና የሰላም አየር እንዲጠናከር ከመንግሥትና ከሕዝብ ጎን በመቆም የበኩላቸውን ኃላፊነት በብቃት እንደሚወጡ ገልጸዋል።
ውይይቱም በብልፅግና ፓርቲ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አሚና አሊይ፣ በወረዳው የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፋጡማ ሰይድ እና በወረዳ ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ዑመር አደም በጋራ መርተውታል።