የወረዳው ጤና ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃጸም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ መድክ አካሄደ --------------------------- ሰንበቴ:ሐምሌ 09/2018 ዓ.ም(ጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬሽን) የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የወረዳው ጤና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ የጤና ኦፊሰሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ባለፉት 12 ወራት በተቋሙ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ተገምግሟል።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አፍራህ ሰይድ የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
ኃላፊዋ በንግግራቸው የአንድ ተቋም ጥንካሬ የሚለካው በዕቅድ አፈጻጸም ብቻ ሳይሆን የተገኘው ውጤት በህብረተሰቡ ጤና ላይ በሚያመጣው ትርጉም ያለው ለውጥ ነው ብለዋል።
አያይዘውም በጽ/ቤቱ ባለፈው በጀት ዓመት የታዩ አበረታች አፈፃጸሞች ቢኖሩም የአፈፃጸም ክፍተቶቻችንን በቀጣይ አመት ለማሻሻል በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።በተለይም የ2019 እቅድ ጥንካሬዎችን በዘላቂነት ለማስቀጠል እና ለነበሩ ክፍተቶች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ ማዘጋጀት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እቅድ ኦፊሰር አቶ ወንድወሰን ወልደየስ የተቋሙን የ2018 በጀት አመት አፈፃጸም ሪፖርት እና የ2019 ዓ.ም እቅድ አቅርበዋል።
በአፈፃጸም ግምገማው ላይ በቀረበው ሪፖርት መሰረት በ2018 በጀት ዓመት ተጨማሪ የማህበረሰብ ፋርማሲ በመክፈት አባላት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉ፣ በጤና ጣቢያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል መታየቱ እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻሉ በጥንካሬ በጥንካሬ ተጠቅሷል።
በሌላ በኩል በጤና ጣቢያዎች የሚስተዋለው የመድኃኒት አቅርቦት ውስንነት፣ አዳዲስ የጤና መድህን አባላትን ወደ ስርዓቱ በማስገባት ረገድ የነበሩ ክፍተቶች እና የተወሰኑ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ችግሮች ለቀጣይ ዓመት ትኩረት የሚሹ መሆናቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።
የግምገማው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክፍተት የተለዮ ተግባራትን እንደ ግብዓት በመጠቀም የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።ሆኖም የጤና ተቋማትን የመፈጸም አቅም ለማሳደግ ተከታታይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል።
በመድረኩ የ2018 ዓ.ም አፈፃጸም ላይ ግምገማ ከተካሄደ ቡኃላ የ2019 በጀት አመት እቅድ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን በዘላቂነት በማጠናከር በኩል ባለሙያ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አጽንኦት በመስጠት በቀጣይ በጀት ዓመት በሁሉም ተግባራት የተሻለ አፈፃጸም ማስመዝገብ እንደሚገባ የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አፍራህ ሰይድ የመድረኩን ማጠቃለያ እና አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።