የበጤ ጤና ጣቢያ የ2018 በጀት ዓመት የ12 ወራት አፈጻጸም አካሄደ ---------------------------- ሰንበቴ:ሐምሌ 08/2018 ዓ.ም(ጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬሽን) በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የበጤ ጤና ጣቢያ የክላስተሩን የ2018 በጀት ዓመት የ12 ወራት የሥራ አፈጻጸም እና የአራተኛ ሩብ ዓመት ግምገማ በዛሬው እለት አካሂዷል።
የጤና ጣቢያው ኃላፊ አቶ አሊ አደም የ12 ወሩን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለተሳታፊዎች አቅርበዋል።
ኃላፊው በሪፖርታቸው እንደገለጹት በ2018 በጀት ዓመት በተለይም በእናቶችና ህጻናት ጤና፣ በወባ መከላከልና ቁጥጥር እንዲሁም በጤና መድን አፈጻጸም ረገድ አበረታች ስራዎች መሰራቱን ገልጸዋል።
አክለውም በበጀት አመቱ ዝቅተኛ አፈጻጸም የታየባቸው ተግባራት በመገምገም ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ ኃላፊ ተናግረዋል።
በሪፖርቱ የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት፣ የሎጂስቲክስ አቅርቦት፣ የሳንባ ነቀርሳ ህክምና፣ የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ፣ የኤችአይቪ መከላከልና ህክምና፣ የደም ግፊት እና የስኳር ህመም ምርመራዎች አፈፃጸሞች ቀርቧል።
በተጨማሪም የወባ መከላከልና ቁጥጥር፣ የትራኮማ በሽታ፣ የጤና መድን ሽፋን፣ የጤና ጣቢያ ለውጥ (Woreda Transformation)፣ እንዲሁም የጤና መረጃ አያያዝ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የጋራ ውይይት ተደርጓል።
በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የወባ መከላከልና ምላሽ ኬዝ ቲም አቶ ጀማል ሀሰን በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ በክላስተሩ የተከናወኑ የድጋፍና ክትትል ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።በመሆኑም በአፈጻጸም ክፍተት የታየባቸውን የስራ ዘርፎች በጋራ በመለየት እና መፍትሄ በማስቀመጥ በቀጣዩ በጀት ዓመት ከዚህ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ሲሉ አቶ ጀማል አሳስበዋል።
የጤና ጣቢያው ሰራተኞች በበኩላቸው በቀረቡት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች ላይ ውይይት በማድረግ ጥንካሬ ያሉትን በመግለጽ በበጀቶ አመቱ ዝቅተኛ አፈጻጸም የታየባቸውን ተግባራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሻሻል ቃል ገብተዋል።
ከ2018 ዓ.ም አፈፃጸም ግምገማ መጠናቀቅ ቡኃላ የተቋሙ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ዕቅዱን በዝርዝር ለመገምገም እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የጋራ ውይይቶችን በማድረግ ተዘጋጆቶ እንዲቀርብ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም በግምገማ መድረኩ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኦፊሰር አቶ ጀማል ሀሰን እና የጽ/ቤቱ ኦፊሰር ወ/ሮ ባንችሁን አበበን ጨምሮ የጤና ጣቢያው ሰራተኞች እና የክላስተር ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች መሳተፋቸውም ታውቋል።