"ከተሞቻችንን የብልጽግና ማዕከላት ለማድረግ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።" - አቶ አህመድ አሊ (የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ)
የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት 28ኛ መደበኛ ጉባኤ 5ኛ ምዕራፍ ጀምሯል። በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸውንና ትልቅ ስኬት መመዝገቡንም ጠቁመዋል።
➲ልማትና መሠረተ ልማት፡- መሰረታዊ የህብረተሰብ ፍላጎቶች ማለትም የውሃ፣መብራትና መንገድ ምላሽ ተሰጥቷል። እንዲሁም 233 ሄክታር መሬት ለማልማት የሚያስችል የመስኖ ፕሮጀክት በብር 393 ሚሊዮን እየተገነባ ነው።
➲ ሰላምና ፀጥታ፡- ከአጎራባች ወረዳዎችና ህዝባዊ ትግሎች ጋር በጋራ በመስራት ሰላሙን ማረጋገጥ ተችሏል።
➲ ግብርናና ምርታማነት፡ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን እርዳታ ከመጠበቅ ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር ሰፊ የትራንስፎርሜሽን ስራ እየተሰራ ነው።